“ፀሐይ፡ የኢትዮጵያ አቪዬሽን አጀማመር” በሚል ርእስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በደማቅ ሥነሥርዓት ተመረቀ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በካፕቴን ዘላለም አንዳርጌ የተዘጋጀውን እና “ፀሐይ የኢትዮጵያ አቪዬሽን አጀማመር” በሚል ርእስ ያሳተመውን መጽሐፍ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ ም በአካዳሚው ቅጥር ግቢ በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡
በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ፕ/ር ባህሩ ዘውዴና ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት ስለመጽሐፉ ታሪካዊና ቅርሳዊ አንድምታ ዳሰሳቸውን አካፍለዋል፡፡








