EAS News

የኢትዮጵያ ዳር ድንበር፤ ያልተቋጨ የቤት ሥራ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬስ ያሳተመውን “የኢትዮጵያ ዳር ድንበር፤ ያልተቋጨ የቤት ሥራ“ የተሰኘ መጽሐፍ አስመረቀ፡፡ በዶክተር በለጠ በላቸው ይሁን ተጽፎ በኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ የታተመው መጽሐፍ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ ምሁራን፣ የተለያዩ የዘርፉ ባለሞያዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ. ም በሂልተን ሆቴል  በይፋ ተመርቋል፡፡ በዚህ ጥራቱን አስጠብቆ መጽሐፉን ባሳተመው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና የሕትመት ወጪውን […]

Read More

የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን (HEART CONVENTION) አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተላለፈ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በየአመቱ እንዲያዘጋጅ የመግባቢያ ስምምነት ነሃሴ 26/2013 ዓም ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጽጌ ገ/ማሪያም ናቸው። በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በቀጣይ […]

Read More

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሴቶችን የዉሳኔ ሰጭነትና የአመራርነት ሚናቸዉን ከፍ ለማድረግ በሥርዓተ ጾታ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙርያ ለአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

አካዳሚዉ ከ International Network for Advancing Science and Policy (INASP) ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከተለያዩ ድርጅቶችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያ ሴቶች በሥርዓተ ጾታ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ የአንድ ቀን የአሰልጣኞች የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና በድረገፅ እና በገፅ ለገፅ  ሰጥቷል፡፡ የአካዳሚዉ የፕሮግራም እና ግራንት ማናጀር አቶ አበበ መኩሪያው በሥልጠናው መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ለተሳታፊዎቹ እንደገለጹት አአካዳሚዉ […]

Read More

የኢፌዲሪ ት/ት ሚኒስቴር እና የኢ.ሳ.አ. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ ሒሳብና ሥነጥበብ ትምህርትን በኢትዮጵያ በጋራ ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ ሒሳብና ሥነጥበብ /STEAM/ ትምህርትን በኢትዮጵያ በጋራ ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ /MoU/ ተፈራረሙ፡፡ የመግባቢያ ሰነዱን የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ የተፈራረሙት፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት […]

Read More

ኢ.ሳ.አ. በአገሪቱ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎችንና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማትን ለማሳደግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የኢፌዴሪ የሳይስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ወደ እውቀት-መር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 5 እስከ 8 /2013 ዓ.ም የተካሄደው የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን (HEART CONVENTION 2021) ይፋዊ የማጠቃለያ ስነስርዓት  በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚው ቅጥር ግቢ በተካሄደበት ወቅት ነበር፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘዉም፣ አካዳሚው በዋነኛነት እየሠራበት ያለው ሳይንስን ባህል በማድረግ በእዉቀት፣ በክህሎት […]

Read More

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የምርምር ሥራዎችን ለፖሊሲ ግብዓትነት ለማዋል የሚያስችል የምርምር ተግባቦት ስልጠና አዘጋጀ፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ለነባርና አዳዲስ ተመራማሪዎች የምርምር ሥራዎቻውን ለፖሊሲ ግብዓትነት ለማዋል የሚያስችላቸው የምርምር ተግባቦት ስልጠና አዘጋጀ፡፡ አካዳሚዉ በፖሊሲ እና በምርምር ውጤቶች መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ዝግጅትና አፈጻጸምን ለማበረታታት ያለመ፣ ከነሐሴ 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት  የሚቆይ የምርምር ተግባቦት (Research Communication) ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናው አካዳሚው ከዚህ ቀደም ያዘጋጀው […]

Read More

የኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ “ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ እና የኢትዮጵያ አብዮት ተሳትፎዬ’’ የተሰኘ መጽሐፍ አስመረቀ፡፡

የኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ ያሳተመውን “ያልታሰበውየሕይወቴፈታኝጉዞእናየኢትዮጵያአብዮት ተሳትፎዬ’’የተሰኘመጽሐፍ አስመረቀ፡፡ በሌተና ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እንግዳ ተጽፎ፣ በአካዳሚ ፕሬሱ የታተመው “ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ እና የኢትዮጵያ አብዮት ተሳትፎዬ” ግለታሪክ ትናንት ሐምሌ 15፣ 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጽ/ቤት ተመርቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ  በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በዕለቱ የተመረቀው የሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ […]

Read More

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የልጆች የሳይንስ ማዕከል አስመረቀ::

የኢትዮጵያ  ሳይንስ  አካዳሚ  በኢትዮጵያ  በአይነቱ  የመጀመሪያ  የሆነውን  የልጆች  የሳይንስ  ማዕከል  አስመርቋል፡፡ አካዳሚዉ ከጀርመን  የባህል ተቋም  እና  ጀርመን  ሀገር  ከሚገኘው  ፌኖሜንታ ሳይንስ ማዕከል ጋር በመተባበር ማቋቋሙም ተገልጿል፡፡ በማእከሉ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዉ  ንግግር  ያደረጉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ  ሚኒስቴር  ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ የኢትዮጵያ መንግስት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት በርካታ ተስፋ ሰጪ […]

Read More

የሰው ኃይል ግንባታ ለሥነ ሕዝባዊ ትሩፋት መሳካት (Realizing Demographic Dividend through Focusing on Human Capital Development)

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሰሞኑን በካፒታል ሆቴል በበይነ መረብና በገጽ–ለገጽ ባዘጋጀዉ የምክክር  መድረክ ላይ በርካታ ሀገራዊ ችግር ፈቺ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል ፡፡ የውይይት መድረኩ የሰው ኃይል ግንባታ ለሥነ ሕዝባዊ ትሩፋት መሳካት (Realizing Demographic Dividend through Focusing on Human Capital Development) በሚል ርዕስ ትኩረቱን በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ አድርጎ ቀርቧል፡፡ […]

Read More

የኢትዮጽያ ሳይንስ አካዳሚ የኢትየጵያ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ-ምርጫ ህዝባዊ ውይይት አካሄደ::

ግንቦት 18 ቀን 2013 (ኢሳአ)፡ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን በማስመልከት ከታሪክ፣ ከሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ከህግ አንጻር ለመዳሰስ የኢትዮጽያ ሳይንስ አካዳሚ የኢትየጵያ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ-ምርጫ ህዝባዊ ውይይት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል አዲስ አበባ በስብሰባ አዳራሽ እና በኦንላይን አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ሶስት አንጋፋ ሙሁራን ከታሪክ፣ ከሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ከህግ አንጻር ምርጫን በማስመልከት የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ […]

Read More