ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የፓናል ውይይት መድረክ

አካዳሚው በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል።

በዚሁ መሠረት #ሀገር_በቀል_እውቀት_ሥርዓት_ለኢትዮጵያ_ዘላቂ_ልማት’’ በተሰኘ የመወያያ ርዕስ የፓናል ውይይት መድረክ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።

አቅራቢዎች፡-

▪️ፕሮፌሰር ዘላለም ልየው

▪️ፕሮፌሰር ሚርጊሳ ካባ

▪️ፕሮፌሰር ዳንኤል ተመስገን

▪️ዶ/ር ታፈሰ መስፍን

የፓናል ውይይቱን ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ ይመሩታል።

ስለሆነም የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ጥሪ የተደረገላችሁ የክብር እንግዶች፣ ጋዜጠኞች፣ ተማሪዎች እና በፓናል ውይይቱ መሳተፍ የምትፈልጉ ዜጎች በሙሉ መድረኩ ክፍት ስለሆነ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በአካል በመገኘት እንድትሳተፉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

🗓 ቀን፦ ሐሙስ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት 12፡00 ሰዓት

📍 ቦታ፦ በአአዩ ቴክኖሎጂና ቢልት ኢንቫይሮመንት ኮሌጅ (አአዩ-5 ኪሎ ካምፓስ) አዳራሽ

በአካል መገኘት ለማትችሉ በዙም (Zoom) ወይም በፖስተሩ ላይ ያለውን QR code በመጠቀም መከታተል ትችላላችሁ።

🔗Zoom link: https://us06web.zoom.us/j/88912129718…

👉Meeting ID: 889 1212 9718

👉Passcode: 802890