News and Updates

News and updates

ዳኛቸው ወርቁ ማን ነው?

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል የደራሲና ገጣሚ  “ዳኛቸው ወርቁ ማን ነው?” በተሰኘ  ርዕስ   የውይይትና  የመታሰቢያ  መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ ማዕከሉ ከአንድ ዓመት በላይ በኮቪድ ወረርሺኝ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች እንቅስቃሴው ተገትቶ የቆየ ሲሆን በዚህ ዓመት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዶ በተቀመጠው አዳዲስ የአሠራር ስልቶች የሥራ እንቅስቃሴውን መጀመሩ ተጠቁሟል። በውይይት መድረኩ […]

Read More

የመጪው 10 ዓመት አገራዊ የባዮቴክኖሎጂ የምርምርና ልማት ረቂቅ መርሐ ግብር

የመጪው 10 ዓመት አገራዊ የባዮቴክኖሎጂ የምርምርና ልማት ረቂቅ መርሐ ግብር ላይ የሚመክር የአንድ ቀን ዓውደ ጥናት ተካሄደ። ማክሰኞ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በአገራዊ የ10 ዓመታት የባዮቴክኖሎጂ የምርምርና ልማት ረቂቅ መርሐ ግብር ላይ የሚመክር የአንድ ቀን ዓውደ ጥናት አካሄደ፡፡ በዓውደ ጥናቱ ከልዩ ልዩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው […]

Read More

ጥምቀት ባህል እና ኪነት ሙያዊና ኪናዊ መድረክ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል “ጥምቀት፣ ባህል እና ኪነት” በተሰኘ ርዕስ ላይ ሙያዊና ኪናዊ መድረክ አከናወነ፡፡ በተለያዩ አገራት በመዘዋወር የኢትዮጵያን ባህልና ትውፊት ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ እየተጋ ያለው የፈንድቃ ባህል ማዕከል መሥራች አቶ መላኩ በላይ ለዓመታት እያካሄደው ስላለው “ፍለጋ’’ ስለተሰኘው የጥምቀት ፌስቲቫል ፕሮጀክቱ ጉዞ እና በከበራ፣ ባህል እና ኪነት ምንነት ዙርያ […]

Read More

ጥምቀት፣ ባህል እና ኪነት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ – ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ቅዳሜ ጥር 14/2014 ዓ.ም ከ7፡00 ጀምሮ “ጥምቀት፣ ባህል እና ኪነት” የተሰኘ ሙያዊና ኪናዊ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡  በዝግጅቱ ላይ ዕውቁ የባህል ተወዛዋዥ መላኩ በላይ – ለዓመታት ፍለጋ ስለተሰኘው የጥምቀት ፌስቲቫል ጉዞው ልምዱን ያጋራናል፣ የጋሞ ባህል ቡድን ትውፊታዊ የባህል ውዝዋዜ ያቀርባል እንዲሁም ከበራ፣ ባህል እና ኪነት ላይ ሙያዊ […]

Read More

የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከልን የሥራ አድማስ በማስፋት የአገሪቱ የባህልና  የሥነ ጥበብ እንቅስቃሴዎች ላይ ሳይንሳዊ አበርክቶ  ለማድረግ በኪነጥበብ እና በባህል ዘርፍ ከሚሠሩ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል.።  የምክክር መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስጀመሩት የአካዳሚው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ የሥነ ጥበባት ማዕከሉ በአዲስ አበባ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተማ […]

Read More

የተማሪዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ውድድር ተካሄደ

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ ማዕከል ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኤሌክትሮኒክስ ቤተ ሙከራዎች በተማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች የምርቃትና ሽልማት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በተግባር ተኮር ሥልጠናው ላይ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች በፈጠራ ችሎታቸው እና በዝንባሌያቸው የተመረጡ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ የቀሰሙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲቀይሩና ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎችን  የመፍጠር ክህሎታቸውን እንዲያበለፅጉ ከስቴም ፓወር ጋር […]

Read More

በሕዝብ ብዛት እና በአገር ዕድገት ትስስር ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሥነ ሕዝብ ዕድገትና አጠቃላይ አገራዊ ዕድገት ግንኙነት  እንዲሁም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የገጽ–ለገጽ  እና የበይነ መረብ የውይይት መድረክ በካፒታል ሆቴል አካሂዷል፡፡ ሕዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡-  የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ-ማርያም በሰጡት ማብራሪያ የሕዝብ ብዛት ለአገር ሀብት መሆኑን ጠቅሰው፤ የሕዝብ ብዛቱ በራሱ ስጋት እንዳይሆን […]

Read More

የ‘‘UNIDO’’ እና የ ‘‘CIRHT’’ የሥራ ሓላፊዎች ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር ተወያዩ

የተባበሩት መንግሥታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (United Nation Industrial Development Organization (UNIDO) እና Center for International Reproductive Health Training (CIRHT) የተሰኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በትብብር በሚስሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡ በአካዳሚው ጽ/ቤት በተካሄደው የሁለቱ ተቋማት እና የአካዳሚው የስራ ሓላፊዎች ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ-ማርያም እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር […]

Read More

የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተወያዩ

የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በትብብር ስለሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡  አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 19/2014: በአካዳሚው ጽ/ቤት በተካሄደው የሁለቱ አካዳሚዎች ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ-ማርያም ስለ አካዳሚው ዋና ዋና የሥራ መርሃ ግብሮች፣ እየሠራቸው ስላሉ ሥራዎች እና በትብብር ሊሠሩባቸው ስለሚችሏቸው ጉዳዮች ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።  ከገለጻው በኋላ ውይይት ተካሂዶ ወደፊት በትብብር  በሚሠሩባቸው […]

Read More

የአውራምባ ማኅበረሰብ ታሪክ እና እሴቶች መሰነድ እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የአውራምባ ማኅበረሰብ አባላት ታሪካቸው እና እሴቶቻቸው በሚሰነዱበት ሁኔታ  ላይ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በአካዳሚው ቅጥር ግቢ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል፡፡ አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 19/2014: የውይይቱ ዓላማ የአውራምባ ማኅበረሰብን አምሳኛ የምሥረታ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ለምርምር የሚጋብዙትን እና መልካም ተመክሮ የሚቀሰምባቸውን የማኅበረሰቡን መልካም አስተሳሰብ፣ ፍልስፍና፣ በጎ ምግባር እንዲሁም ጠንካራ የሥራ፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል ለአገራችንና ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ክፍል […]

Read More