በአክብሮትተጋብዘዋል!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ  ገለጻና ውይይት መድረክ

አካዳሚው በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ገለጻና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

አሁንም በትምህርት ነክ ጉዳዮች ላይ በየወሩ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ የገለጻና የውይይት መርሐግብሮች ሁለተኛውን መርሐግብር ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያበተሰኘ ርእስ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ አቅራቢነት በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ አወያይነት ያካሂዳል።

መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንድሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።