የማይቀሩበት ልዩ ዓለም አቀፋዊ የሥዕል አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ከINTER-ART Foundation -Aiud, Romania ጋር በመተባበር ከ100 ሀገራት የተሰባሰቡ 100 ሥዕሎችን የያዘ ዓለም አቀፍ ተጓዥ ኤግዚቢሽን “CULTURAL IMPRESSIONS” በሚል ርዕስ ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ በይፋዊ ተከፍቶ እስከ ጥር 27 2015 ዓ.ም ድረስ ለዕይታ ይቀርባል፤ የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ በሰዓሊ ታምራት ስልጣን ሲሆን፣ ይህ አውደ ርዕይ” መነሻ ዓለም አቀፍ የሥዕል ሲምፖዚየም” /Origin international Art Symposium/ አካል ነው፡፡ ከአውደ ርዕይው ጎን ለጎን በአካዳሚው ውስጥ ከጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም አንስቶ ለ5 ቀናት የሚቆይ ልዩ የቀጥታ የሥዕል ክዋኔ (Live Art Performance) ከ25 ሀገራት በመጡ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሠዓሊያን ይቀርባል፡፡ በተጨማሪም በሥነ ጥበብ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ እና ሙያዊ ውይይቶች ይደረጋሉ፡፡
በመሆኑም ጥር 26 2015 ዓ.ም በ11፡00 ሰዓት ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ እንዳሉ የኢን.ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ በሚገኘው ቅጥር ግቢያችን በመገኘት በዝግጅቱ እንድትታደሙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡