የአማካሪ ውል ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሳንዶካን ደበበ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰላማዊ ተግባር የምትገነባውን የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ቦታ በጥናት ለመለየት የሚያስችል ሲሆን ጥናቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው መስፈርቶችን የተከተለ፣ ደህንነቱ አስተማማኝ እና ተስማሚ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየት ይረዳል።






