Walking Tall Educational Theatre በአዲስ አበባ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ካደረገው Palaeontological Scientific Trust (PAST) ጋር በመተባበር Walking Tall Educational Theatre የተሰኘ ሳይንሳዊ ወርክሾፕ ዛሬ በአዲስ አበባ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ካደረገው Palaeontological Scientific Trust (PAST) ጋር በመተባበር Walking Tall Educational Theatre የተሰኘ ሳይንሳዊ ወርክሾፕ ዛሬ በአዲስ አበባ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል፡፡

2

የአፍሪካን ቀደምት ግኝቶችና ማንነትን በሳይንሳዊ መረጃዎች በማስደገፍ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ  እንዲሁም የአፍሪካውያንን ክብር፣ ማህበራዊ ትስስርና የተፈጥሮ እንክብካቤ፣ አንድነትን፣ የጋራ መስተጋብራችንን ስለማጠንከር የሚያስተምረው፤ ፍፁም ማራኪ በሆኑ የአካል እንቅስቃሴዎች የተሞላው ሳይንሳዊ ቴአትር እየታየ በምሁራንና በተማሪዎች ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

1

ዝግጅቶቹ በልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው አርብ የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ህብረተሰቡ ስለቀደምት የሰው ዘር መገኛ አፍሪካ ያለውን ግንዛቤ በእጅጉ እንዲያሰፋና የዓለም ህብረተሰብ ተፈጥሮን ከማውደም እንዲቆጠብ፣ ወደግጭት የሚያመራውን የሀብት አጠቃቀም ፍትሀዊ እንዲያደርግና አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና ዓለም-አቀፋዊ መስተጋብሩን እንዲያጠነክር እያዝናና የሚያስተምር ዝግጅት ነው፡፡

በመሆኑም ይህን መርሐ-ግብር መላዉ ህብረተሰብ አርብ ሚያዝያ 12/2010 ዓ.ም ከ9፡00-10፡30 ድረስ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ግቢ (5 ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም) በሚገኘውን የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *