ህብረተሰቡ ስለቀደምት የሰው ዘር መገኛ አፍሪካ ያለውን ግንዛቤ በእጅጉ እንዲያሰፋና የዓለም ህብረተሰብ ተፈጥሮን ከማውደም እንዲቆጠብ፣ ወደግጭት የሚያመራውን የሀብት አጠቃቀም ፍትሀዊ እንዲያደርግና አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና ዓለም-አቀፋዊ መስተጋብሩን እንዲያጠነክር እያዝናና የሚያስተምር ዝግጅት ነው፡፡
በመሆኑም ይህን መርሐ-ግብር መላዉ ህብረተሰብ አርብ ሚያዝያ 12/2010 ዓ.ም ከ9፡00-10፡30 ድረስ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ግቢ (5 ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም) በሚገኘውን የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡