Research Communication for greater impact!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በምርምር ሥራዎችና በፖሊሲ መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ዝግጅትና አፈጻጸምን በማሻሻል ላይ ያተኮረ የአምስት ቀን የምርምር ተግባቦት ( Research Communication) ስልጠና ከነሐሴ 03 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ማዶ ሆቴል አዘጋጅቷል፡፡
ስልጠናውም በሥነ ሕዝብና ልማት ዘርፍ ላይ የሚገኙ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ የምርምር ሥራዎች ላይ የሚሳተፉ ነባርና ጀማሪ ባለሙያዎችን ስትራጂያዊ የምርምር ተግባቦት እውቀትና ክህሎት ለማዳበር ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡