የድኅረ ምረቃ ትምህርት በኢትዮጵያ፤ መስፋፋት፣ የመግቢያ መስፈርት እና የሰልጠና ጥራት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ  ገለጻና ውይይት መድረክ

አካዳሚው በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ገለጻና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

አሁንም በትምህርት ነክ ጉዳዮች ላይ በየወሩ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ የገለጻና የውይይት መርሐግብሮች ሦስተኛውን መርሐግብር የድኅረ ምረቃ ትምህርት በኢትዮጵያ፤  መስፋፋት፣  የመግቢያ መስፈርት እና የሰልጠና ጥራትበተሰኘ ርእስ በዶክተር በላይ ሐጎስ  አቅራቢነት በፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ ማርያም አወያይነት ያካሂዳል።

መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንድሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።