“#አፈወርቅ_ተክሌ” የስዕል ትርዒት ሊከፈት ነው

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴንጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል የእውቁን ሰዓሊ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን 10ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ በማስመልከት የስዕል ትርዒት አዘጋጅቷል፡፡ ትርዒቱ አርብ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም በ9፡30 በይፋ ተመርቆ ተከፍቶ ሚያዚያ 8 ቀን 2014 ዓ.ም በልዩ መርሃ ግብር የሚዘጋ ይሆናል፡፡

“#አፈወርቅ_ተክሌ” የስዕል ትርዒትበዚህ የስዕል ትርኢት ቁጥራቸው በርካታ የሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ የሥነጥበብ ሥራዎች ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን ቅዳሜ ሚያዚያ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሰዓሊው ሙያዊና ሰዋዊ ማንነነት ላይ ያተኮረ ውይይት ይከናወናል፡፡ በውይይት ሀሳብ መነሻም በሰዓሊ ጌታ መኮንን እና በደራሲ ዓያልነህ ሙላት ይቀርባል፡፡ አጠቃላይ ዝግጅቶቹ ሁሉ በነጻ ለህዝብ ክፍት የሚሆኑ ሲሆን የሥነጥበብ ወዳጆችና አድናቂዎች ትርዒቱን እንዲጎበኙ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

አድራሻ፡- ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል 500 ሜትር ገባ ብሎ፡፡