ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የ6ኛው ዙር ‘የበጎ ሰው ሽልማት’ የሳይንስ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኑ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራች አባል እና የቦርድ አባል ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በሠሯቸው ሙያዊ ሥራዎችና ባበረከቷቸው አስተዋጽዖዎች የ2010 ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት የሳይንስ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኑ፡፡ ነሐሴ 27/2010 ዓ.ም. በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በተደረገው የሽልማት ሥነ ሥርዓት በተለያዩ ዘርፎች በሙያቸውና እና በዕውቀታቸው በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በፈጠራና ቴክኖሎጂ እድገት፣ በኪነ ጥበብ እና በሥነ ምግባር ለውጦች እንዲመጡ አስተዋጽዖ ላደረጉ ግለሰቦች የዓመቱ በጎ ሰው በማለት ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ በዚህ ዓመታዊ የዕውቅና መስጫ መርሐ ግብር ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በ2010 ዓ.ም. በየዘርፉ ከታጩት ውስጥ በሳይንስ ዘርፍ የተሸለሙ ሲሆን፤ ፕሮፌሰሩ ላለፉት 50 ዓመታት ሳይንሳዊ ዕውቀት በኢትዮጵያ እንዲጎለብት ላደረጉት መልካም ተግባር ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው የሽልማቱ አዘጋጅ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራች አባል እና የቦርድ አባል ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በሠሯቸው ሙያዊ ሥራዎችና ባበረከቷቸው አስተዋጽዖዎች የ2010 ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት የሳይንስ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኑ፡፡

ነሐሴ 27/2010 ዓ.ም. በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በተደረገው የሽልማት ሥነ ሥርዓት በተለያዩ ዘርፎች በሙያቸውና እና በዕውቀታቸው በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በፈጠራና ቴክኖሎጂ እድገት፣ በኪነ ጥበብ እና በሥነ ምግባር ለውጦች እንዲመጡ አስተዋጽዖ ላደረጉ ግለሰቦች የዓመቱ በጎ ሰው በማለት ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ በዚህ ዓመታዊ የዕውቅና መስጫ መርሐ ግብር ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በ2010 ዓ.ም. በየዘርፉ ከታጩት ውስጥ በሳይንስ ዘርፍ የተሸለሙ ሲሆን፤ ፕሮፌሰሩ ላለፉት 50 ዓመታት ሳይንሳዊ ዕውቀት በኢትዮጵያ እንዲጎለብት ላደረጉት መልካም ተግባር ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው የሽልማቱ አዘጋጅ ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት በተደረጉት የበጎ ሰው ሽልማቶች የኢትጵያ ሳይንስ አካዳሚ አባል የሆኑት ዶ/ር እሌኒ ገብረመድኅን በኢኮኖሚው መስክ አዲስ መንገድ በማሳየት (1ኛው ዙር፣ 2005 ዓ.ም.)፣ ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ በሳይንስ ዘርፍ እና አቶ ደሳለኝ ራሕመቶ በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ (3ኛው ዙር፣ 2007 ዓ.ም.)፣ ዶ/ር መላኩ ወረደ በሳይንስ እና ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ (4ኛው ዙር፣ 2008 ዓ.ም.) እንዲሁም ኤመሬተስ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በማኅበራዊ ጥናት እና ኤመሬተስ ፕሮፌሰር ንጉሤ ተበጀ በሳይንስ ዘርፍ (5ኛው ዙር፣ 2009 ዓ.ም.) መሸለማቸው ይታወቃል፡፡

የኢትጵያ ሳይንስ አካዳሚም አባላቱ ለማበረሰቡ እያደረጉ ያለውን ሙያዊ አስተዋጽዖ አጠናክረው እንዲቀጥሉ እያበረታታ፤ የ6ኛውን ዙር የሳይንስ ዘርፍ አሸናፊ አባን እና መላውን ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *