ጥምቀት፣ ባህል እና ኪነት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ – ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ቅዳሜ ጥር 14/2014 ዓ.ም ከ7፡00 ጀምሮ “ጥምቀት፣ ባህል እና ኪነት” የተሰኘ ሙያዊና ኪናዊ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

 በዝግጅቱ ላይ ዕውቁ የባህል ተወዛዋዥ መላኩ በላይ – ለዓመታት ፍለጋ ስለተሰኘው የጥምቀት ፌስቲቫል ጉዞው ልምዱን ያጋራናል፣ የጋሞ ባህል ቡድን ትውፊታዊ የባህል ውዝዋዜ ያቀርባል እንዲሁም ከበራ፣ ባህል እና ኪነት ላይ ሙያዊ ሀሳቦችን እናነሳለን፡፡

 በዝግጅቱ ለመታደም የፈለጉ ሁሉ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ጠብቀው እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡

Location: https://bit.ly/3qKJGa8