የSTEM ማዕከል ርክክብ ተደረገ

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሒሳብ ትምህርት ዘርፎች ላይ አጋዥ የሆነ ተግባራዊ ትምህርት መስጫ ማዕከል ዛሬ ሐምሌ 1/2011 ዓ.ም ርክክብ ተደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥር የሚገኘው የሳይንስ ማዕከል ሳይንስን እና ሳይንሳዊ አሠራርን በኅብረተሰቡ ውስጥ ለማስፋፋት በማሰብ የተለያዩ የማስተማሪያ፣ የቤተ-ሙከራና የምርምር ዩኒቶች እያደራጀ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ዩኒቶች መካከል አንዱ የሆነው…

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሒሳብ ትምህርት ዘርፎች ላይ አጋዥ የሆነ ተግባራዊ ትምህርት መስጫ ማዕከል ዛሬ ሐምሌ 1/2011 ዓ.ም ርክክብ ተደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥር የሚገኘው የሳይንስ ማዕከል ሳይንስን እና ሳይንሳዊ አሠራርን በኅብረተሰቡ ውስጥ ለማስፋፋት በማሰብ የተለያዩ የማስተማሪያ፣ የቤተ-ሙከራና የምርምር ዩኒቶች እያደራጀ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ዩኒቶች መካከል አንዱ የሆነው የSTEM (በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና የሒሳብ ትምህርት ዘርፎች) ማዕከል ከSTEM Synergy Inc,. ከተባለ ተመሳሳይ ዓላማ ካለው ድርጅት በተደረገ ድጋፍ የተደራጀው ማዕከል ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

ማዕከሉ በዋናነት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና የሒሳብ ትምህርት ዘርፎች ላይ በማተኮር ከ2ኛ ደረጃና መሠናዶ ተማሪዎች ሥርዓተ-ትምህርት ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነ የሳይንስ ማዕከሉ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኤፍሬም እንግዳወርቅ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች በመማሪያ ክፍል ውስጥ የቀሰሟቸውን ንድፈ-ሀሳባዊ ዕውቀቶች በተግባ እንዲፈትሹ እድል ከመስጠቱም በላይ ‹‹ለከፍተኛ ትምህርት በማዘጋጀት እና የወጣቶችን የፈጠራ ክህሎት በማዳበር ረገድ ምቹ የሆነ የፈጠራ አካባቢም እንዲሆን የማድረግ ሥራም እየተሠራ ይገኛል›› ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

እንደዚህ አይነት ተቋማትን በማስፋፋትና በዘመናዊ ቁሳቁስ በማደራጀት የኅብረተሰቡን እና ኅብረተሰቡ የሚገለገልባቸውን አሠራሮች ሳይንሳዊ ማድረግ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት ከሚያደርጋቸው ጥረቶች ጎን ለጎን ሳይንሳዊ ዕውቀትን በስፋት ማስተዋወቅ እንደሀገር ወደተሸለ ነገ የሚወስድ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ በጋራ መሥራት እንዳለበት ተጠቅሷል፡፡

112

የSTEM Synergy Inc,. ፕሬዚደንት አቶ ፀጋዬ ለገሰ በሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን ‹‹የኢትዮጵያን የሳይንስና ቴክኖሎጂን ለማሻሻል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ወጣቶችና ሕፃናት ላይ ቀድሞ መሥራትና መኮትኮት ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

የSTEM Synergy Inc,. የSTEM ማዕከሉን ለማደራጀትና ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ የቁሳቁስና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረጉ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡ የምስክር ወረቀቱን የአካዳሚው የቦርድ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ለSTEM Synergy Inc,. ተወካይ አስረክበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *