የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘’የፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፡– አተገባበሩ፣ ተግዳሮቶቹና መጻኢ ዕድሉ’’ በተሰኘ አገራዊና ወቅታዊ አጀንዳ ላይ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እና ተቋማትና ያሳተፈ የውይይት መድረከ ጥር 25/2011 ዓ.ም በግዮን ሆቴል አካሂዷል፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ‘’የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሥርዓት አመሠራረት፣ ፋይዳውና ቀጣይ አቅጣጫዎቹ’’ በዶ/ር አሰፋ ፍስሐ፣ ‘’የፊስካል ፌዴራሊዝም አተገባበር በኢትዮጵያ፤ ስኬቱና ክፍተቱ’’ በዶ/ር ሰለሞን ንጉሤ፣ ‘’የኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት ሕገመንግሥታዊና የአተገባበር ክፍተቶች እና ተግዳሮቶች’’ በዶ/ር አስናቀ ከፋለ እና ‘’ስኬታማ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ አማራጮች፣ ተፈላጊ ለውጦችና መጻኢ ዕድሎች’’ በዶ/ር አበራ ደገፋ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ሃሳቦችን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የቀረቡትን የውይይት መነሻ ጽሑፎች እዚህ ላይ ተጭነው ያገኛሉ