የኢ.ሳ.አ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ (STEM) ማዕከል ሽልማት ተበረከተለት

የአካዳሚው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ (STEM) ማዕከል በኮምፒዩተር እና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ ያሰለጠናቸው ተማሪዎች ዘንድሮ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው በሰባተኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፌይር በመሳተፍ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን ለውድድር አቅርበዋል፡፡

ዘንድሮ ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ሕዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በቆየው ዝግጅት 195 በተማሪዎች የተሠሩ የፈጠራ ስራዎች ለውድድር ቀርበዋል፡፡

በዚህም ውድድር በአካዳሚው የSTEM ማዕከል ሰልጣኞች የቀረበው የተቀናጀ የቤት ደህንነት መጠበቂያና መቆጣጠሪያ ሥርዓት ‘‘Integrated Home Security System’’ አንደኛ በመውጣት ላፕቶፕ ኮምፒዩተር የተሸለመ ሲሆን ሌላው በተማሪዎች የቀረበው የCarbon dioxide Capturing Machine የሶስተኝነት ደረጃን በማግኘት የታብሌት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በዚሁ ዝግጅት ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ከስድሳ በላይ የሚሆኑ የSTEM ማዕከላት መካከል የአካዳሚው የSTEMማዕከል ሶስተኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡