የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል።
በዚህ መሰረት መሠረት ” የመሬት መንቀጥቀጥና የዕሳተ-ገሞራ ፍንዳታ አደጋ በኢትዮጵያ፣ ስጋት እና መፍትሄዎች’’ በተሰኘ የመወያያ ርእስ የፓናል ውይይት መድረክ
በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።
አቅራቢዎች፡-
- ፕ/ር አታላይ አየለ – የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በኢትዮጵያ፣
- ፕ/ር አስራት ወርቁ – የግንባታ ኮድ ክለሳ በኢትዮጵያና አሁን ያለበት ሁኔታ፣
- ፕ/ር ተገኘ ገ/ እግዚአብሔር-''የከተማ አካባቢ እቅድና አስተዳደር፣ ዋና ሃሳቦች፣ ዓለም ዓቀፍ ልምዶችና
ተሞክሮዎች”
አወያይ፡-
- ፕ/ር ገዛኸኝ ይረጉ
መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው ወይም ከዚኽ በታች በተጠቀሰው የዙም አድራሻ በቀጥታ እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
Zoom Link: https://us06web.zoom.us/j/83792558786…
Passcode: 871333





