የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የትውልድ አደራ የተሰኘ መጽሐፍ ያስመርቃል

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአካዳሚው ፕሬስ አማካኝነት ያሳተመውን የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምን የትውልድ አደራ የተሰኘ ግለ-ታሪክ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአካዳሚው ፕሬስ አማካኝነት ያሳተመውን የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምን የትውልድ አደራ የተሰኘ ግለ-ታሪክ መጽሐፍ …

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአካዳሚው ፕሬስ አማካኝነት ያሳተመውን የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምን የትውልድ አደራ የተሰኘ ግለ-ታሪክ መጽሐፍ መጋቢት 7/2009 ዓ.ም በዋናው ጽ/ቤት በይፋ ያስመርቃል፡፡

የኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ስር ካሉት ክፍሎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ምርምርን ማኸዘብና ሳይንሳዊ ዕውቀታችንን ወሰን የሚያሰፋልን ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የምርምር ውጤቶች ማሣተም ከፕሬሱ ዋንኛ ዓላማዎች መካከል ይገኛሉ፡፡

የፕሬሱ ዋና ተግባር ከአካዳሚው አባላትና ከውጭ ለኅትመት የሚቀርቡ ረቂቆችን ተቀብሎ፤ በአባላቱ አስገምግሞ በግምገማው መሠረት አስፈላጊውን ማሻሻያ አድርጎ ማሣተምና ለሕዝብ ማድረስ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ የአሥር መጻሕፍት ረቂቆች እንዲያሣትም ቀርበውለት ባስገመገመው መሠረት በተለያዩ ምክንቶች አምስት ረቂቆች ለጸሐፊዎቹ ተመላሽ ተደርገዋል፡፡ አካዳሚው ዛሬ ለምርቃት የቀረበውን ጨምሮ ሦስት መጻሕፍት አሣትሟል፡፡

በሚቀጥሉት ጥቂት ወራትም፣ የህያው ምሥጢር በሚል ርዕስ በፕ/ር ሽብሩ ተድላ የተዘጋጀውና በመሠረታዊ ሳይንስ ግንዛቤ ዙሪያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለኅትመት ይበቃል፡፡ እንደዚሁ ግምገማው የተጠናቀቀለት በአቶ ሰይፉ መታፈሪያ የተዘጋጀውና በምሥራቅ ሐረርጌ አካባቢ ያሉ የኦሮሞ ሕዝብ ነዋሪዎች የሥራ ላይ ግጥሞቻቸው ዙሪያ የተሠራ የፎክሎር ምርምራዊ ጽሑፍ ለኅትመት እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

ይህ የትውልድ አደራ በሚል ርዕስ ለምርቃት የበቃው መጽሐፍ፣ በልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም የተዘጋጀ የሕይወት ታሪካቸው ሲሆን፤ ባለታሪኩ የተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች አስተዳደርና የሥራና መገናኛ ሚኒስቴር ሚንስትር ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡ መጽሐፉ በእነዚህ ኃላፊነቶቻቸው ወቅት ከሠሯቸው ሥራዎች በተጨማሪ ከልጅነታቸው እስከ አሁን ድረስ ያለፉበትን የልጅነት ዕድገት፣ የቤተሰብ ታሪክ፣ የፖለቲካ ውጣ ውረድና ማኅበራዊ ሕይወትን የሚዳስስ ከመሆኑ ባሻገር፤ ከአብዮቱ ጋር በተያያዘ ልዑል ራስ በትጥቅ ትግል ያሳለፉበትን ዘመን የሚያካትት ዝርዝር ስለያዘ፤ ለዘመኑ ታሪክ እንደቀዳማይ ምንጭ ተደርጎ የሚቆጠር ነው፡፡

መጽሐፉ 304 ገጾች ያሉት ሲሆን፣ 115 ፎቶግራፎች፣ አራት ካርታዎች እና አንድ ንድፍ አካቷል፡፡ መጽሐፉ በሽፋን ዋጋ 170 ብር በየመጽሐፍት መደብሮች እንደሚገኝ አካዳሚው ይገልፃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *