የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ የሥራ ቡድን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በራስ አምባ ሆቴል ለአንድ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ያለምፀሓይ መኮንን አካዳሚው እያከናወናቸው ስላላቸው ተግባራት፣ ዋና ዋና የሥራ መርሃ ግብሮች እና ስለየተለያዩ ፕሮጀክቶች ገለጻ አድርገዋል።

በስብሰባው የሥራ ቡድኑን ቀደም ሲል በሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩት ፕሮፌሰር አታላይ አየለ በቡድኑ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችንና የተገገኙ ውጤቶችን ለቡድኑ አባላት አቅርበዋል።

አዲሱ የሥራ ቡድኑ ሊቀመንበር  ፕሮፌሰር ትዕግስቱ ኃይሌ ለቡድኑ አባላት ባደረጉት ገለጻ፣ የቡድኑን ተልዕኮ፣ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ የአፈፃፀም ሁኔታ አጠቃላይ ግምገማ እና ቀጣይ በልዩ ትኩረት መሠራት ስለሚገባቸው ተግባራት አብራርተዋል።

 

 

 

 

 

የሥራ ቡድኑ አባላት  እስካሁን ባለው የሥራ ሂደት ኮቪድን ጨምሮ ላጋጠሙ በርካታ ችግሮች ምላሾችን በመስጠት ረገድ የታዩ ለውጦች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው ወደፊት ለመራመድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

የሥራ ቡድኑ የአባላቱን ተሳትፎ በማጎልበት ከተለያዩ አለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በማሳደግ የሥራ ቡድኑንና በጥቅሉም የአካዳሚው ተልዕኮ  ማሳካት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች  ላይ መክረዋል።