የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አደረጉ

በአገር-አቀፍ ደረጃ ዛሬ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበላይነት ሲያስተባረው በነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ችግኝ ተከላ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች፣ ዓለም-አቀፍ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ሠራኞቹ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

ከመርሐ-ግብሩ መጠናቀቅ በኋላ ችግኞቹን መንከባከብ አስፈላጊ እንደሆነም ተሳታፊ ሠራተኞች ገልፀዋል፡፡  

2

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *