የኢትዮጵያ ሥነሕዝባዊ ትሩፋትን ይመልከቱ|Watch Ethiopia’s Demographic Dividend

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከፖፑሌሽን ሪፈረንስ ቢሮ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ሥነሕዝባዊ ትሩፋት የተሰኘ የቪዲዮ ገለጻ አዘጋጅቷል፡፡ አካዳሚው በሥነሕዝባዊ ትሩፋትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ የሚደረጉ ውይይቶች በመረጃ ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑና ዐውዳዊ ይዘት እንዲኖራቸው ለማገዝ ይህንን ቪዲዮ አዘጋጅቷል፡፡ቪዲዮው የኢትዮጵያ ፖሊሲ አውጪ አካላትና መላ ህብረተሰቡ፣ ስለ ሥነሕዝባዊ ትሩፋት እንዲሁም ኢትዮጵያ የትሩፋቱ ተጠቃሚ ለመሆን ስላላት ዕድል ያላቸውን ግንዛቤ ለማዳበር ይረዳል የሚል ተስፋ አለን፡፡
ቪዲዮውን ለተለያዩ ታዳሚዎች ለማቅረብ ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የ ቪዲዮ ገለጻ መምሪያ በእንግሊዘኛና በአማርኛ ተዘጋጅቷል፤ መምሪያው የተለያዩ ታዳሚያንን ለመድረስ በግብዓትነት እንዲያገለግል ግልጽ በሆነና በተብራራ መልኩ ቀርቧል:: ገለጻውን በፈለጉት መንገድ ማቅረብ ለሚፈልጉ ሰዎችም ያለትረካ በፓወርፖይንት ተዘጋጅቷል፡፡
ሥነሕዝባዊ ትሩፋትንና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለሚያቀርቡት ገለጻ ቪዲዮውን ወይም ፓወርፖይንቱን እንዲጠቀሙ እናበረታታለን፡፡

=================================================================

EAS, in collaboration with the Population Reference Bureau, has produced a video presentation titled Ethiopia’s Demographic Dividend. EAS produced the video with the objective of facilitating evidence-based and contextualized policy dialogue on the demographic dividend and related issues in Ethiopia. It is our hope that the video will enhance policymakers’ and people’s understanding of the demographic dividend and Ethiopia’s prospect of achieving it.

The video is prepared with English and Amharic presentation guideline for professionals who wish to present the video to different audiences. The guideline is a succinct and readable document serving as an aid to reach different audiences with the presentation. The video is also prepared in a PowerPoint format for people who may wish to present the video without the narration.

We encourage professionals to use the video and/or PowerPoint when giving a presentation on the demographic dividend and related issues.

 

የኢትዮጵያ ሥነሕዝባዊ ትሩፋት ቪዲዮን እዚህ ይመልከቱ     

      > Watch the video here

ቪዲዮ ገለጻ መምሪያውን ያውርዱ:                                           Download video presentation guideline:

እንግሊዘኛ ቪዲዮ ገለጻ መምሪያ                                       >English video presentation guideline

አማርኛ የቪዲዮ ገለጻ መምሪያ                                           >Amharic video presentation guideline