“የአካባቢ ጥበቃና የደን ልማት የዕቅድ፣ የአፈጻጸምና የአደረጃጀት ቅንጅት”

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ አካዳሚያዊ እና ሳይንሳዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን
ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ወርሐዊ የሳይንሳዊ ገለፃና
ውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ የመሰብሰቢያ
አዳራሽ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት አካዳሚው ሐሙስ የካቲት 26 2012 ዓ/ም ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ “የአካባቢ ጥበቃና
የደን ልማት የዕቅድ፣ የአፈጻጸምና የአደረጃጀት ቅንጅት
” በተሰኘ አጠቃላይ ርዕስ ሥር የፓነል ውይይት
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፕዩቴሽናል ኮሌጅ አዳራሽ (4 ኪሎ ግቢ) አዘጋጅቷል፡፡  
በውይይቱ ላይ ሦስት ዕውቅ ባለሙያዎች በአካባቢ ጥበቃና የደን ልማት ዙሪያ በተለያዩ ርሶች ገለጻ
ያደርጋሉ። እነዚህም፤
1. “የኢትዮጵያ የደን ሀብት ዘላቂ ልማት፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና መልካም አጋጣሚዎች”
አቅራቢ – ዶ/ር አደፍርስ ወርቁ (በአካባቢ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የደን ዘርፍ ልማት
ፕሮግራም ትግበራ ከፍተኛ የደን ባለሙያ)

2. “የኢትዮጵያ የደን ሀብት ከማኅበራዊ፣ ከኢኮኖሚያዊ እና ከአየር ንብረት ለውጥ አንጻር
የሚጫወተው ሚና”
አቅራቢ ዶ/ር ይግረማቸው ስዩም (በዓለምአቀፉ የአረንጓዴ ዕድገት ተቋም አማካሪ)

3. “የደን ዘርፍ ተቋማዊ አደረጃጃት እና ቅንጅታዊ አሠራር”
አቅራቢ – ዶ/ር ሀብተማሪያም ካሳ (በዓለም አቀፉ የደን ምርምር ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ)

4. “በኢትዮጵያ የደን ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን (ስር ሰደድ ለውጥ) አስፈላጊነትና የትግበራ ፍኖተ ካርታ”
አቅራቢ – አቶ ጥላዬ ንጉሴ (በአካባቢ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የደን ዘርፍ
ትራንስፎርሜሸን ዩኒት ዳይሬክተር)

ሥለሆነም በውይይቱ እና የገለጻ መድረኩ እንዲሳተፉ በክብር ተጋብዘዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *