የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራ ከግሉ ዘርፍ እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርምር ጋር መተሳሰር አለበት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የቴክኖሎጂ ሽግግር በኢትዮጵያ በተሰኘ ርዕስ 39ኛውን የሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረክ የካቲት 28/2011 ዓ.ም አካሄደ፡፡

በዚህ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢንዱስትሪያል ምሕንድስና ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የቦርድ አባል በሆኑት በፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ገለፃ ቀርቦ በተሳታፊዎች ምርምር ተደርጎበታል፡፡ በመድረኩ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው የቴክኖሎጂ ሽግግር አንድን የዳበረ ቴክኖሎጂ ካደገበት ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክሎጂያዊ አውድ ወስዶ ወደ ሌላ ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክሎጂያዊ አውድ ማላመድ እንደሆነ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የቴክኖሎጂ ሽግግር በኢትዮጵያ በተሰኘ ርዕስ 39ኛውን የሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረክ የካቲት 28/2011 ዓ.ም አካሄደ፡፡

በዚህ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢንዱስትሪያል ምሕንድስና ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የቦርድ አባል በሆኑት በፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ገለፃ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመድረኩ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው  የቴክኖሎጂ ሽግግር አንድን የዳበረ ቴክኖሎጂ ካደገበት ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክሎጂያዊ አውድ ወስዶ ወደ ሌላ ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክሎጂያዊ አውድ ማላመድ እንደሆነ ገልፀዋል።

በአብዛኛው የቴክኖሎጂን ድምዳሜ (የተሳሳተ ትርጉም) የመስጠት ማለትም፦ ቴክኖሎጂን እንደ ማሺን ወይም መሳሪያ ብቻ  የማየት እና አንዳንድ ጊዜ የሳይንስ ጽንሰሐሳብን ለብቻው እንደ ቴክኖሎጂ የመው የግንዛቤ ክፍተቶች ይስትዋላሉ ያሉት አቅራቢው፤ ነገር ግን ቴክኖሎጂ ማለት ሸቀጦችን ወይም አገልግሎቶችን ለማምረት እና ለማሰራጨት ብሎም ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያገለግሉ የእውቀት፣ የክህሎት፣ የመሣሪያዎች፤ የልምድና ተቋማዊ  አወቃቀር ስርዓትን ጭምር እንደሚያካትት ጠቅሰዋል፡፡

የቴክኖሎጂ እድገትና ውድድር ዓለምን በተለያዩ ደረጃዎች በማዋቀሩ፣ ምርቶች የሚመረቱባቸውንና አገልግሎቶች የሚቀርቡበትን አዳዲስ ስልቶችና  ማሻሻያዎችን ማድረጊያው ቀጥተኛው መንገድ በመሆኑ ቴክኖሎጂ የልማትና አጠቃላይ የኅብረተሰብ ለውጥ የጀርባ አጥንት እንደሆነም በገለፃቸው አንስተዋል፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማረጋገጥም በፕሮፌሰር ዳንኤል አገላለፅ ‹‹ተጠቃሚው ቴክኖሎጂውን በደንብ አውቆ በሚገባ ሲጠቀምበት ለአካባቢው ተስማሚ እንዲሆን ሲያደርግ፤ ማሻሻያ (ሞዲፊክ) ሲያደርግ እና በተቀባዩ ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክሎጂያዊ አውድ ውስጥ ማላመድና ማሰራጨት›› ሲችል እንደሆነና፣ ዋና ዋናዎቹ አመልካቾችም ተቋማዊ መሰረተ ልማት፤ ግልጽ የሆነ የልማት ግቦች፤ ተስማሚ የሆነ ተቋማዊ ማዕቀፍ፤ የሠለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት፤ እና  ለተቋሞችና ህጎች ምቹ ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ አስተዳደራዊ አካሄዶችን ማቋቋም ሲቻል ነው ብለዋል፡፡

የገለፃው አቅራቢም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች ዕይታ አንፃር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ፣ የስኳር ልማት፣ የሲሚንቶ፣ የኃይል ማመንጫ፣ የትራንስፖርት እና የምግብና የመጠጥ ማምረቻ ዘርፎች ሲሆኑ፤ በቀጣይም የቴክኖሎጂ ሽግግር በኢትዮዽያ ዘለቄታዊ እድልን ስለሚወስንና ይህ ደግሞ ሰፊውን የሐብት ስርጭት ስለሚያበረታ፤ አሁን ያሉት እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች፣ የግሉ ኢንቨስትመንት እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ማስተሳሰር ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ መሆኑን አንስተዋል

ፕሮፌሰር ዳንኤል አክለውም በኢትዮጵያ ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንቅፋቶች ካሏቸው ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ ሥራዎች እና ኢንዱስትሪዎች በተናጥል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የትም እንደማያደርስ አፅንዖት በመስጠት ገልፀዋል።

2

ከገለፃው በኋላ በተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በዉይይቱም ወቅት በአግባቡ ያልተሳሰሩ አካላት ጥረት የተሻሻሉ መሣሪያዎች፥ ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶችን ለማኅበረሰቡ በብቃት የሚያደርሱ መሆን ሲገባችው በምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ መፍጠራቸው፤ የጥናትና ምርምር ተቋማት የምርምር ውጤት በወቅቱ ወደተግባር ያለመቀየር፣ የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን ለሥራው ያላቸው ብቃትና ዝግጁነት አናሳ መሆን፥ የሥርዓተ ትምህርት ዓይነቶች እና የሙያ ደርጃዎች ከሥራው ዓለም ጋር አለመጣጣምና የኢንዱስትሪውን ፈጣን ፍላጎት ያማከሉ አለመሆን እና አብዛኛዎቹ ኢንተርፕራይዞች ከሚጠበቅባቸው ደረጃ በታች እየሠሩ መሆናቸው ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።  ይህ የአቅም ውስንነት በጥቅሉ የኢንዱስትሪ ተቋማት ደካማ ንድፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል ብቃት እና ብቃት ያላቸው አስተዳዳሪዎች እጦት፤ የግብዓት እጥረት አካላዊ እና ተቋማዊ መሠረተልማቶች ውስንነትም ሽግግሩን ደካማ እንዳደረገውም ተወያዮች አንስተዋል፡፡

3

በመሆኑም በአቅራቢው እና በተወያዮች የቴክኖሎጂ ሽግግርና ዕድገትን በጠንካራ መሠረት ላይ ለማቆም ይረዳሉ የተባሉት ምክረ-ሃሳቦችም ቀርበዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-

  • የቴክኖሎጂ ልማት አቅጣጫ ጠቋሚ አገራዊ ንድፍ/ፖሊሲ መቀየስ፤
  • በዘርፉ ፖሊሲ አውጪዎችን ሊያማክርና አቅጣጫ ሊያስይዝ የሚችል የምሑራን ቡድን (Technology Gatekeepers) ማደራጀት፤
  • ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ምርት የመተካት ስራ በፖሊሲ ደረጃ ቀዳሚ  ዓላማ በማድረግ በአጭር ጊዜ አመርቂ የቴክኖሎጂ ዕድገት ማምጣት፤
  • የአገር በቀል እውቀቶች እና ቴክኖሎጂዎች ለመለየትና ለመገምገም የሚረዱ ዘዴዎችን እና ሥርዓቶችን ማመቻቸት፤
  • የአገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል የሚያግዝ የመሰረተልማትየብድር አገልግሎት እና የምርምር በጀት ማመቻቸት፤
  • በምሕንድስና እና ቴክኖሎጂ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ምርምሮች አገር በቀል እውቀቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል ዐቅም እንዲፈጥሩ ትኩረት  ማድረግ፤ እና
  • በከፍተኛ ትምህርት ተቋምት ምርምር፣ በግሉ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትና በመንግስት የሚደረገው የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር ሥራ የተሳሰረ እንዲሆን ማድረግ ወሳኝ የወደፊት አቅጣጫ መሆን ይኖርበታል በማለት የወደፊት አቅጣጫዎች ተጠቁመዋል፡፡

ውይይቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሲቪል ምሕንድስና ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራች አባል እንዲሁም በአካዳሚው ውስጥ የምሕንድስናና ቴክኖሎጂ የሥራ ቡድን ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ የመሩት ሲሆን፣ ከተለያየ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተገኙ ከ170 በላይ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡

12

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *