ውድ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ወርሐዊ ገለፃና የውይይት መድረክ ተከታታዮች!እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ አገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ወርሐዊ ገለፃና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየዉን ይህንኑ መርሐ ግብር ለማስቀጠል በመጪው ዓርብ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም “ፌዴራሊዝምና ጎሣዊ አደረጃጀት፣ ከኢትዮጵያ ተሞክሮ ምን ትምህርት ተገኘ?” በተሰኘ ርዕስ ላይ የገለጻና የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡በዚህም መድረክ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ገለጻ ያደርጋሉ። የገለጻና የውይይት መርሐ ግብሩ ቀደም ሲል ሊካሄድ ከታቀደበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግቢ በእሸቱ ጮሌ አዳራሽ ወደ አካዳሚው ዋና ጽ/ቤት የተዛወረ ሲሆን ዓርብ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ውይይቱን በ ‘‘Ethiopian Academy of Sciences’’ ፌስቡክ ገጽ በቀጥታ መከታተል የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። አድራሻ፡- ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል 500 ሜትር ገባ ብሎ፡፡