የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የዘመናዊነት አስተውሎት በዘመኑ ትውልድ ዕይታ

በፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ አሠናጅነት በኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ የታተመው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን የዘመናዊነት አስተሳሰብ የሚተርከው መጽሐፍ ”የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የዘመናዊነት አስተውሎት በዘመኑ ትውልድ ዕይታ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወጣት ምሁራን መስከረም 25/2010 ዓ.ም ውይይት ተካሄደበት፡፡

በፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ አሠናጅነት በኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ የታተመው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን የዘመናዊነት አስተሳሰብ የሚተርከው መጽሐፍ ”የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የዘመናዊነት አስተውሎት በዘመኑ ትውልድ ዕይታ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወጣት ምሁራን መስከረም 25/2010 ዓ.ም ውይይት ተካሄደበት፡፡ 

Book Cover

በዶ/ ዮናስ አሽኔ፣ / መሰለ ተሬቻ እና አቶ ፋሲል መራዊ አማካኝነት የቀረበው ገለጻ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን የዘመናዊነት አስተውሎት፣ ሂስና አዲስ ዕይታን አስመልክቶ በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ብላቴን ጌታ ኅሩይ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ዓለምአቀፍ ጉዞዎች የኃያላን አገራት የዘመናዊነት ፍኖት በዋናነት ቁስ አካላዊ ዕድገት ላይ የተመረኮዘ እንደሆነ፤ ይህ የስልጣኔ ቅኝትም የሌሎችን ባህልና ፍልስፍና በማጥፋት ልዕልና ለመያዝ ያለመ እንደሆነ አቶ ፋሲል መራዊ አብራተዋል፡፡ በታላቁ የአድዋ ድል በመነሳሳት ኢትዮጵያን ለማዘመን ከተደረጉ ጥረቶች ውስጥ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ የጉዞ ማስታወሻ ምርምርና ፍልስፍና ትልቁን ሚና ይጫወታልም ብለዋል፡፡ የጉዞ ማስታወሻው በወቅቱ ከነበሩ ሐይማኖታዊና የጦር አውድማ ድርሳናት በእጅጉ የተለየ የዘመናዊነት ዕይታዎችን ያስተዋወቀ ነው፡፡

አቅራቢዎቹ አክለውም በተለምዶ መዘመን ከከተሜነት እና የምዕራባውያንን ዕሴቶች የሙጥኝ ከማለት ጋር ብቻ ሲቆራኝ ይስተዋላል፡፡ ነገር ግን ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ስልጣኔን ከአገር ባህልና ትውፊት ማጣጣም እንዲሁም ዘመናዊነት ከአገር በቀል ጥበብ የሚጀምር እንደሆነ የጠለቀ ግንዛቤ ነበራቸው፡፡ ይህ እይታ የተለየ ዐውድ ያለውን የአውሮፓ ስልጣኔ ብቻ ከመጎምዠት ይልቅ ኢትዮጵያ ያላትን የዕውቀት፣ የቋንቋ፣ የፍልስፍና፣ የዘመናዊነትና የግብረገብነት ፈለጎችን ማጥናትና መልሶ መጠቀም ያሻል በማለት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ይሞግታሉ፡፡ የኢትዮጵያን ማህበራዊ ግስጋሴ እና ዘመናዊነት ታሪክ ለሚያጠኑ ለታሪክ፣ ለቋንቋ፣ ለባህል፣ ኢኮኖሚ እና ፍልስፍና ተመራማሪዎች ጠቃሚ መጽሐፍ እንደሆነም ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *