የቡና ተክል ዕድገትና ምርት ከአየር ንብረት ለውጥ አንፃር

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ቡና አምራች አገር ከመሆኗም ባሻገር ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማምጣት ትታወቃለች፡፡ የቡና የውጪ ንግድ ለበርካታ አመታት የኢኮኖሚው ዋልታ በመሆንም ትልቅ…

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ቡና አምራች አገር ከመሆኗም ባሻገር ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማምጣት ትታወቃለች፡፡ የቡና የውጪ ንግድ ለበርካታ አመታት የኢኮኖሚው ዋልታ በመሆንም ትልቅ አገራዊ ሚና ሲጫወት ቆይቷል፤ እየተጫወተም ይገኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ የቡና ተክል ዕድገትና ምርት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሥነምሕዳሩ እየተጎዳ ምርቱም እየቀነሰ እንደሚሄድ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ችግሩ ሥር ከመስደዱ አስቀድሞ መፍትሔ ማበጀት አስፈላጊ ስለሚሆን፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ  የቡና ተክል ዕድገትና ምርት ከአየር ንብረት ለውጥ አንፃር በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ ገለፃ አዘጋጅቷል፡፡

በገለፃው፡

  • የቡና አብቃይ አካባቢዎች ስነምሕዳር እና የአመራረት ሂደት መስተጋብር  (በዶ/ር ታደሠ ወ/ማርያም)
  • የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በቀጣይ ዐሥርት ዓመታት እና መወሰድ የሚኖርባቸው ተስማሚ እርምጃዎች (በፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው) እና
  • በአገር አቀፍና በክልሎች የተዘረጉ የቡና ልማት ሥራ አቅጣጫዎች (በአቶ ብርሃኑ ፀጋዬ)

ዋና ዋና የፓናሉ መወያያ ንዑሳን ርዕሶች ይሆናሉ፡፡

አካዳሚው ሁሉም ሕብረተሰብ የዚህ ሳይንሳዊ ገለፃ ተሳታፊ እንዲሆን ይጋብዛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *