ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ:-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና ፕ/ር ተከተል ዮሀንስ;-የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር የስምምነት ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡
የስምምነት ሰነዱ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኩል የሚተገበሩ በአገር ዉስጥ የሚታተሙ ጆርናሎችን በተቀመጠ ስታንደርድ መሠረት የመገምገም ፤ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር አመራሮች እና ለጆርናል ኤዲተሮች የአቅም ግንባታ ስልጠናን የመስጠትን ጨምሮ ሌሎች ዝርዝር ተግባራት ተካተዉበታል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከላይ ለተጠቀሱ ጥቅል አገልግሎቶች ከሰባት ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ብር በላይ ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለዉ የሥራ ግንኙነት ቀደም ብሎ የተጀመረ መሆኑና በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኩል አገር በቀል ጆርናሎችን መመዘን የሚያስችል ስታንደርድ ተዘጋጅቶ ከ2012 ዓም አመልካቾች መካከል 16 ጆርናሎች መስፈርቱን አሟልተዉ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል እዉቅና ማግኘታቸዉ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ዘርፎች በሳይንስ ባህል ግንባታ ላይ የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ነዉ፡፡“