የኢትዮጵያ ወጣቶች ሳይንስ አካዳሚ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እንዲሁም ፈረንሳይ ሀገር ከሚገኘው አፕሳ (APSA) ጋር በመተባበር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ለወጣቶች አዘጋጅቷል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች ሳይንስ አካዳሚ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እንዲሁም ፈረንሳይ ሀገር ከሚገኘው አፕሳ (APSA) ጋር በመተባበር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ለወጣቶች አዘጋጅቷል፡፡
የፈጠራ ውጤቶቹ ዘላቂ የልማት ግቦችን መሰረት በማረግ በአካባቢያዊ፣ በማህበራዊ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤና ወይም በየትኛውም የማህበረሰብ የኑሮ ሁኔታ ላይ መፍትሄን የሚያመጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሀሳብ (ፕሮጀክታቸውን) ወይም ፕሮቶታይፕ እስከ ሀምሌ 24 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፡፡
ሁሉም ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ማጠናቀቂያ በሚዘጋጀው ለህዝብ ክፍት በሚሆን አውደ-ርዕይ ላይ በመሳተፍ ስራቸውን የማስተዋወቅ ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡
የውድድሩ ሽልማቶች
1ኛ ደረጃ ለወጣ የ 2,500 ዩሮ ሽልማት እና 3,000 ዩሮ ድረስ የሚፈጅ የአንድ ወር የምርምር ስልጠና በታወቀ የቴከኖሎጂ ላቦራቶሪ
2ኛ ደረጃ ለወጣ የ 1,500 ዩሮ ሽልማት እና 3,000 ዩሮ ድረስ የሚፈጅ የአንድ ወር የምርምር ስልጠና በታወቀ የቴከኖሎጂ ላቦራቶሪ
3ኛ ደረጃ ለወጣ የ 1,000 ዩሮ ማበረታቻ
የውድድሩ መዝጊያ ቀን – ሀምሌ 24/2010 ዓ.ም
አመልካቾች በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ድረ-ገጽ www.eas-et.org ላይ በመግባት http://challengest.
የኢትዮጵያ ወጣቶች ሳይንስ አካዳሚ