የሰው ኃይል ግንባታ ለሥነ ሕዝባዊ ትሩፋት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሰሞኑን በካፒታል ሆቴል በበይነ መረብናገጽለገጽ ባዘጋጀዉ የምክክር  መድረክ ላይ በርካታ ሀገራዊ ችግር ፈቺ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል ፡፡

የውይይት መድረኩ የሰው ኃይል ግንባታ ለሥነ ሕዝባዊ ትሩፋት መሳካት (Realizing Demographic Dividend through Focusing on Human Capital Development) በሚል ርዕስ ትኩረቱን በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ አድርጎ ቀርቧል፡፡

በዕለቱ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ሙያዊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ተመራማሪዎቹ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የታለመውን ግብ ለማሳካት ንቁ፣ ጤናማ፣ አምራች ሰብአዊ ካፒታል ማፍራትና ሥነ ህዝባዊ ሽግግርን (Demographic Transition) ማፋጠን ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ 

የምክክር  መድረኩን በንግግር የከፍቱት  የአካዳሚዉ ፕሬዝደንት  ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የታለመውን የ10 አመት የሀገሪቱ መሪ እቅድ ግቡን እንዲመታ ከጤና፣ ከትምህርትና ሌሎች የልማት ዘርፎች ጋር የተጣጣመ የሥነ ህዝብ ፖሊሲ በተገቢው መተግበር የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው የሀገሪቱን አጠቃላይ የልማትና እድገት ጉዞ ለማፋጠን ወደ ሥራ የሚገባው ህዝብ በሰው ኃይል ገበያ ላይ የሚፈለግ እውቀት፣ ክህሎትና  መልካም ስብእና እንዲኖረው ማድረግና በዚህ ልክ የሥራ እድል ማስፋት እንደሚያስፈልግ አክለዋል፡፡

በሀገሪቱ ቀደም ሲል የነበረውን ከፍተኛ የሞትና የውልደት ምጣኔ በማሻሻል ወደ ዝቅተኛ የውልደትና የሞት ምጣኔ ደረጃ በማድረስ እየታየ ያለውን ለውጥ ማፋጠን ስራ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ እንደሚገባ በምክክር መድረኩ የተሳተፉ ምሁራን አሳሰበዋል፡፡

አያይዘውም የሰው ኃይል ግንባታ እና ሥነ ሕዛባዊ ትሩፋትን ለማሳካት በየዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት በይነዘርፋዊ ዘዴ (intersecoral approach) የተከተለ መሆን እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

ሕዝብ የአንድ ሀገር ሀብትና የልማት ባለቤት ቢሆንም ከሀገሪቱ የመሰረተ ልማት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አቅርቦትና ከአጠቃላይ እድገት ጋር ያልተጣጣመ የህዝብ ብዛት ለኑሮ ውድነት፣ ለአካባቢ ብክለትና ለአየር ሚዛን መዛባት መንስኤ መሆኑን በመገንዘብ የሥነ ሕዝባዊ ሽግግርን  ከማሻሻል ጎን ለጎን እንደ ትምህርት፣ ጤናና የስራ ዕድል ፈጠራ በመሳሰሉ ዋና ዋና ዘርፎች ላይ በትኩረት በመስራት ለአሁንና ለቀጣይ የሰው ሀብት ግንባታ እንዲሁም ለሥነ ሕዝባዊ ትሩፋት መሳካት ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ  ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሥነ ሕዝባዊ ትሩፋት ማሳካትና ለሰው ኃይል ግንባታ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

The Ethiopian Academy of Sciences has recently organized a hybrid policy dialogue on key national development issues at the Capital Hotel

The dialogue was organized on the topic of Realizing Demographic Dividend through Focusing on Human Capital Development, laying its emphasis on education, health and job creation. It convened researchers, policy makers and experts from research and academic institutions. The Experts presented problem solving study results and they highlighted the importance of creating active, healthy, productive human capital and accelerating demographic transition to achieve the national goal of making Ethiopia a beacon of Africa’s prosperity.

Opening the forum, the President of the Academy, Prof. Tsige Gebre-Mariam, said that in order to accelerate the overall development and growth of the country, it is necessary to equip the people who are entering the workforce with knowledge, skills and good attitude that fits the labor market with the necessary effort in the key areas such as health and education.

He also mentioned that the platform will also contribute to the government’s effort to implement the 10-year perspective development plan by addressing the existing challenges and gaps while also providing policy implications.

According the Experts, balancing the demography in line with health, education and other development sectors has an irreplaceable role to play in achieving the country’s 10-year development plan to make Ethiopia a beacon of African prosperity.

The panelist pointed out that, although population is engine for development, the imbalance between the population and development on the other hand will limit access to and quality of basic social services, bring environmental degradation, high inflation and climate change.

They also emphasized on the importance of a concerted effort from all parties at stake and application of intersectoral approach while working on both demographic dividend and human capital development. Additionally, participants urged on the need to revise the national population policy in support of the development the country is aspiring.

Executive Director of the Ethiopian Academy of Sciences, Professor Teketel Yohannes finally called on all stakeholders for a collaborated engagement in the effort or realizing demographic dividend and human capital development.

media coverages on our dialog held on July 9,2021.
https://www.youtube.com/watch?v=tGf0D9hiVE4