የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተወያዩ

የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በትብብር ስለሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡

 አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 19/2014: በአካዳሚው ጽ/ቤት በተካሄደው የሁለቱ አካዳሚዎች ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ-ማርያም ስለ አካዳሚው ዋና ዋና የሥራ መርሃ ግብሮች፣ እየሠራቸው ስላሉ ሥራዎች እና በትብብር ሊሠሩባቸው ስለሚችሏቸው ጉዳዮች ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

 ከገለጻው በኋላ ውይይት ተካሂዶ ወደፊት በትብብር  በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።

በመጨረሻም የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ ልኡካን ቡድን የአካዳሚውን የሳይንስ ማእከል  እና የተለያዩ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።