ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ተከበረ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አዲስ አበባ ከሚገኘው የባንግላዴሽ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን የካቲት 15/2011 ዓ.ም በአካዳሚው ጽ/ቤት አከበረ፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አዲስ አበባ ከሚገኘው የባንግላዴሽ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን የካቲት 15/2011 ዓ.ም በአካዳሚው ጽ/ቤት አከበረ፡፡

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው በክብር እንግዳነት የተገኙ ሲሆን፤ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ከመግባቢያነት በዘለለ ባህልም ቅርስም ስለሆነ መጠበቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ አክለውም ‹‹እውነትን እና የራስን ማንነት ለመናገር የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቅርቡ መንገድ ነው፤ የአፍ መፍቻ ቋንቋ እውነት ስለሆነ›› በለማት የአፍ መፍቻ ቋንቋን የመጠቀምን አስፈላጊነት ጠቅሰዋል፡፡

2

       የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ፅጌ ገብረማርያም በመርሐ ግብሩ ላይ ዕለቱን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል፡፡ ‹‹በአፍ መፍቻ ቋንቋ መናገርም ሆነ መማር ዓለማቀፋዊ መብቶች ሲሆኑ፣ አዳዲስ አስተሳሰብን እና ዕውቀትን ለመገንዘብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቅርብ ነው›› በማለት የዕውቀት እና የመጠየቅ አቅም ከቋንቋ ጋር የተዛመደ መሆኑን ገለጸው፣ አካዳሚውም በኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀትን ለማስፋፋት የሚያግዝ የሳይንሳዊ ቃላት ስያሜና ፍቺ መዝገበቃላት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ለታዳሚዎች አብራርተዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቅኝ አገዛዝ እና ሉላዊነት ጋር በተዛመደ መልኩ የተለያዩ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች እና ዘዬዎች መጥፋት አሳሳቢ መሆኑም ተደጋግሞ ተነስቷል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ የተለያዩ አገራት ዜጎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የአገራቸውን ሙዚቃዎች እና ክዋኔዎችም ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡

3

በዚህ በዓለም የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን አከባበር ላይ በርካታ የመካከለኛው፣ የደቡብ ምስራቅ እና የሩቅ ምሥራቅ እስያ አገራት ኤምባሲዎች፣ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተወካዮች፣ የአካዳሚው አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *