የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ሰኔ 18/ 2014 ዓ.ም “ዐጀሚ ሥነጽሑፍ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ አሰናድቷል፡፡ በመድረኩ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዐረብኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መምህርና የትምህር ክፍሉ ኃላፊ አቶ ሐሰን ሙሐመድ (የPhd ዕጩ) ገለጻ ያደርጋሉ፡፡ ምን ያህሎቻችን ስለዐጀሚ ሥነጽሑፍ እናውቃለን? በኢትዮጵያ ታሪክና ሥነጽሑፍ ውስጥ ያለውን ቦታስ ምንያህል መረጃው አለን? በነዚህ እና በሌሎች ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዙ ጠንካራ ውይይቶች ይከናወናሉ፡፡ ዝግጅቱ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 ጀምሮ በአካዳሚው ግቢ ይከናወናል፡፡ መገኘት ለሚፈልጉ ሁሉ በሰዓቱ በመገኘትና መታደም ይችላሉ፡፡ አድራሻችን፡- ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ 500 ሜትር ገባ ብሎ፡፡