ኢትዮጵያ፡ በምናቦች አጽናፍ በተሰኘ ርዕስ ላይ ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚያዘጋጀው ወርሃዊ የውይይት መድረክ ‹‹ኢትዮጵያ፡ በምናቦች አጽናፍ›› በተሰኘ ርዕስ ላይ ጥቅምት 29/2011 ዓ.ም በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

አቅራቢው አቶ ይኩኖአምላክ የውይቱን መነሻ በሁለት ፈርጅ በመሰደር አቅርበዋል—የተስፋ ምናብና የቀቢጸ-ተስፋ፡፡ በሁለቱም ፈርጆች ከታሪክ፣ ከሚዳሰሱና ከትውፊታዊ ቅርሶች፣ ከስነ-መለኮት፣ ከተፈጥሮ፣ እንዲሁም ከሃይማኖት ትርክትና የማመሳከሪያ ሰነዶች በማጣቀስ አቅራቢው የዳሰሱ ሲሆን፤ መሠረታዊ የገለፃውን መነሻና መዳረሻውን የትላንቱ ኢትጵያዊ ታላቅነትና የገናናነት ምናብ አድማስ ከዛሬው በቀቢጸ-ተስፋ ከተሞላው ኢትዮጵያዊ ምናብ ጋር በማነፃጸር ትነተና ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚያዘጋጀው ወርሃዊ የውይይት መድረክ ‹‹ኢትዮጵያ፡ በምናቦች አጽናፍ›› በተሰኘ ርዕስ ላይ ጥቅምት 29/2011 ዓ.ም በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ  ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

አቅራቢው አቶ ይኩኖአምላክ የውይቱን መነሻ በሁለት ፈርጅ በመሰደር አቅርበዋልተስፋ ምናብና የቀቢጸ-ተስፋ፡፡ በሁለቱም ፈርጆች ከታሪክ፣ ከሚዳሰሱና ከትውፊታዊ ቅርሶች፣ ከስነ-መለኮት፣ ከተፈጥሮ፣ እንዲሁም ከሃይማኖት ትርክትና የማመሳከሪያ ሰነዶች በማጣቀስ አቅራቢው የዳሰሱ ሲሆን፤ መሠረታዊ የገለፃውን መነሻና መዳረሻውን የትላንቱ ኢትጵያዊ ታላቅነትና የገናናነት ምናብ አድማስ ከዛሬው በቀቢጸ-ተስፋ ከተሞላው ኢትዮጵያዊ ምናብ ጋር በማነፃጸር ትነተና ቀርቧል፡፡

‹‹ትርጓሜ አንድምታ ፈርጀ ብዙ ትርጉምና ምልከታ ያለው ሲሆን፣ በየዘመኑ የተለያዩ ትርጉሞችን መፍጠር ያስችላል›› ያሉት አቶ ይኩኖአምላክ፤ በዚህም ‹‹ኢትዮጵያ የምናብ ውጤት ናት››  ይላታል፡፡ ለዚህ ምልከታ ማሳያ ያሏቸውን እንደ ክብረ ነገሥት፣ የላሊበላ ኪነ ሕንፃ፣ ቅኔ እና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጣቀሻነት ያቀርባሉ፡፡ ‹‹ክብረ ነገሥት በታሪክ ትርጓሜ፣ በመንግስት ምሥረታ እና ለለግፉአን መጠጊያ በማድረግ የኢትዮጵያውያንን ምናብ ያሰፋዋል፡፡ ኢትዮጵያን ቀዳሚዋ የስደተኞች መዳረሻና መጠጊያ ሲያደርጋት፣ ማስፋት፣ ማዋሐድ፣ ማዛመድ የዘመነ ክብረ ነገሥት ኢትዮጵያውያን ቀዳሚው ምናብ ነው›› በማለት አቅራቢው ይገልጹታል። ከዚህ በላይ ግን ክብረ ነገሥት የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን የተበየነበት፣ የኢትዮጵያ ታሪክ በኢትዮጵያውያን መምህርነት የተሰበከበት ክሥተት እንዲሆን አስችሏልም በማለት ክብረ ነገሥት ለኢትዮጵያዊው ከፍታ ምርኩዝ መሆኑንም አቶ ይኩኖአምላክ በገለፃው ጠቅሰውታል፡፡

የላሊበላ ኪነ ሕንጻ እና ዕሳቤ ሌላው የኢትዮጵያውያን የታላቅነት ምናብ ውጤት እንደሆነ አቶ ይኩኖአምላክ ይናገራሉ፡፡ ‹‹የላሊበላ መታነጽ በክብረ ነገሥት የተቀመጠውን የኢትዮጵያ ምናብ የበለጠ የሚያጠናክር፣ ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን በኢትዮጵያ በመመሥረት በክብረ ነገሥት የተገለፀው ኢትዮጵያዊ ምናብ ቀጣይነት›› እንደሆነ በገለፃው ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል የክብረ ነገስት መንትያ የሆነው ፍትሐ ነገሥት በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት እና የታላቅነት ምናብ ላይ ወሳኝ ቦታ የነበረው መጽሐፍ እንደሆነም አቅራቢው አንስተዋል፤ ‹‹ክብረ ነገሥት ለኢትዮጵያ ያስታጠቃትን የታላቅነት የምናብ ትጥቅ ያስፈታ ነበር›› በማለት ሞግተዋል፡፡ ከአስተዳር አልፎ በእድገት እና የራስን ትርክትና ዕውቀት ከመንበሩ አውርዶ የበታችነት ስነ ልቦና ፈጥሯልም ባይ ናቸው አቶ ይኩኖአምላክ፡፡ ይኸም ለትውልዱ ከፍተኛ የምናብ መቀማት አውርሶታል፤ፍትሐ ነገሥት ኢትዮጵያውያንን ስለራሳቸው ቦታ ሌሎች እንዲተምኑላቸው የተስማሙበት – የተረቱበት – ምናባቸውን የተቀሙበት መጽሐፍም ነው በማለት ገለፃውን አቅርበዋል።

Participants

የቀረበውን ገለፃ መነሻ በማድረግ ተሳታፊዎችም ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰንዝረዋል፡፡ በኢኮኖሚ ዕሳቤ፣ በትምህርት ንድፍ፣ በአስተዳደር የራስን በመተው በሌሎች ምናብ የመዳከር ታናሽነት፤ የዛሬው ኢትዮጵያዊ በታላቅነት ላይ የተመሠረተውን የቀደመ ምናቡን ከአጠገቡ አጥቶታል፤ ኢትዮጵያዊው ዛሬ ስለራሱ ከሌሎች መስማት – ሌሎች በሰጡት ደረጃ ተደላድሎ መቀመጥ መለያው ኾኗል፤ በቀደሙት ዘመናት በመጻሕፍት ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊ የተባለው ኹሉ የዛሬውን ኢትዮጵያዊ አይመለከትም ቢባል ‹‹ነው›› ብሎ የሚሞግትበት አቅም አጥቷል፤ ምናቡን ተቀምቷልና በማለት በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

አቅራቢው አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡም፤ ኢትዮጵያዊ ምናቡን ስለተቀማ እነዚህ የኢትዮጵያ የስሟ መሠረት ለኢትዮጵያዊው መነሻ ምርኩዝ እንዳይኾኑት አድረገውት ኖረዋል፡፡ ስለሆነም የዛሬው ኢትዮጵያዊ ወደቀደመ ምናቡ ለሚያደርገው ምልሰት ታሪኩን የመተረክ፣ የመናገር፣ የመጻፍ መብቱን በእጁ ማድረግ ይኖርበታል በማለት ተሳታፊዎች እና አቅራቢው በሰጡት አስተያየት ውይይቱ ተጠናቅቋል፡፡

የገለፃውን መርሐ-ግብር ፕ/ር ባዬ ይማም የመሩ ሲሆን፤ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች እና የብዙኃን መገናኛ አባላት ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *