“አስር ዓመት ሙዚቃዊ ጉዞ” የውይይት መድረክ ከሞሰብ ባንድ ጋር

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 20/ 2014 ዓ.ም በሞሰብ የባህል ሙዚቃ ቡድን ላይ ያተኮረ “አስር ዓመት ሙዚቃዊ ጉዞ” የተሰኘ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የጃዝ አምባ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መሥራችና ዳይሬክተር ሙዚቀኛ ዓብይ ወልደማርያም የውይይት መነሻ ሃሳብ የሚያቀርብ ሲሆን የሙዚቃ ቡድኑም ጥዑመ ዜማዎችን ያስደምጠናል፡፡ ከዚያም ባለፈ በ10 ዓመታት የሙዚቃ ቡድኑ ጉዞና አበርክቶቱ ላይ ሙያዊ ውይይት ይከናወናል፡፡ ዝግጅቱ ከ7፡30 አንስቶ በአካዳሚው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን መገኘት ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት ነው፡፡

አድራሻ፡- ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል 500 ሜ ገባ ብሎ፡፡