አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ማዋል ይቻላል

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአገር ዕድገት ያለው አስተዋፅዖ በተሰኘ ርዕስ ጥር 30/2011 ዓ.ም. የሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ለአገር ዕድገት ማዋል ስለሚቻልበት ሁኔታ የኅብረተሰቡን እና የፖሊሲ አውጪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ በተዘጋጀው ወርሐዊ መድረክ የአይኮግ ቤተ ሙከራ (iCog Labs) መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአገር ዕድገት ያለው አስተዋፅዖ በተሰኘ ርዕስ ጥር 30/2011 ዓ.ም. የሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን  ለአገር ዕድገት ማዋል ስለሚቻልበት ሁኔታ የኅብረተሰቡን እና የፖሊሲ አውጪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ በተዘጋጀው ወርሐዊ መድረክ የአይኮግ ቤተ ሙከራ (iCog Labs) መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

1

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ለዕድገታቸው ያዋሉ የዓለማችን አገራት እየተበራከቱ በመምጣታቸው በብዙ አገራት እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ለአብነትም ካናዳ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ እስራኤል እና ቻይና ግንባር ቀደም እንደሆኑ አቅራቢው አብራርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ አቶ ጌትነት ገለፃ ከ48 በመቶ በላይ የሚሆኑት የዓለማችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና ትግበራ ጀማሪ ኩባንያዎች ቻይና ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው በገለፃው ወቅት ተነስቷል፡፡

የሰው ልጆች ወይም እንስሳት ሊከውኗቸው የሚችሏቸውን ተግባራት በተቀላጠፈ፣ በፈጠነና በተሻለ የጥራት ደረጃ በመፈጸም ውጤታማ የዕድገት መንገድ በመሆኑ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤታማ የሳይንስ ዕመርታ እንደሆነም ተብራርቷል፡፡

ለኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በሚስማማ መልኩ መጠቀም ስለሚቻልበት ሁኔታ በገለፃው ተነስቶ፣ በባንክና ኢንሹራንስ አሠራር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በኢንዱስትሪ ምርት ሂደትና ሥርጭት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መተግበር የሚቻል ስለሆነ፣ ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት የተሻለውና አዋጭ መንገድ እንደሆነም አቶ ጌትነት ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መስፋፋት እና ጥቅም ላይ መዋል ሥራ አጥነትን ሊያስከትል ይችላል የሚለው ስጋት ከተወያዮች የተነሳ ሲሆን፣ ‹‹ዓለም በከፍተኛ ውድድር ላይ ስለሆነ ለአለም ገበያ የሚቀርብ ጥራት ያለው እና በዋጋ ተወዳዳሪ ምርት ማምረት እና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ችግር በፍጥነት መቅረፍ አማራጭ አይኖረውም፤ ሰዎች በፈጠራና ምርምር ሥራዎች ላይ በማተኮር የጉልበት ሥራ አካል የሆኑት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መተካት ይኖርበታል›› ብለዋል አቶ ጌትነት፡፡

2

በኢፌዲሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በኢትዮጵያ ማሳደግና ለዕድገት ማዋል በመንግስት አንዱ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ ለታዳሚው ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስቴር ደኤታው አስተያየት መንግስት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን  በአግባቡ ለዕድገት ማዋል እንዲችል ‹‹የጠራ ፖሊሲ ከመቅረጽ ጀምሮ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በመደበኛ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት መንግስት አቅጣጫ አስቀምጦ እየሠራ ይገኛል›› ብለዋል፡፡

 

በሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረኩ ከ240 በላይ የሚሆኑ ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

3

የውይይቱን ቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *