መጋቢት 27 ሐሙስ ከ11፡00 ጀምሮ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (5 ኪሎ) ግቢ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ
መጋቢት 27 ሐሙስ ከ11፡00 ጀምሮ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (5 ኪሎ) ግቢ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ
ሱስ የሚያስይዙ ዕፆች፣ መድሀኒቶችና የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦችን መጠቀምን ተከትሎ የሚከሰቱ የጤና፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች የሰው ልጅ የሚቸገርባቸው አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ናቸው፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ አባል በሆኑ የአለም ጤና ድርጅትና መሰል ድርጅቶች ትኩረት ከሚሰጣቸው ችግሮች ይመደባሉ፡፡
- ለመሆኑ እነዚህ ችግሮች በሀገራችን ምን መልክ አላቸው?
- ውጤታማ የመፍትሄ እርምጃዎች የሚባሉትስ ምን ምንን ያካትታሉ?
- በሀገራችን በተጨባጭ ችግሩን ለመከላከል በመወሰድ ላይ ያሉ እርምጃዎች ምንድናቸው? ምን ውጤት አመጡ? ምን ምን ጠንካራና ደካማ ጎኖች አሉት? ከችግሩ በዘላቂነት ለመውጣት ወደፊት ምን መደረግ አለበት?
በነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በዘርፉ የዳበረ ዕውቀት ባካበቱ ምሁር ሳይንሳዊ ገለጻ የሚደረግ ሲሆን ከተሰታፊዎች በሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ሰፊ ውይይት ይደረጋል፡፡ የውይይት መድረኩ ግንዛቤ የሚያስጨብጥና ጠቃሚ የመፍትሄ አማራጭ መንገዶችን የሚያሳዩ ሃሳቦች ይንጸባረቁበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡