‹‹ሦስቱ የካቲቶች›› የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ በይፋ ተከፈተ

የካቲት 1888 | የካቲት 1929 | የካቲት 1966

ዐውደ ርዕዩ ከየካቲት 1 – 30/2011 ዓ.ም ይቆያል

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥር የሚገኘው የብላቴንጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ‹‹ሦስቱ የካቲቶች›› የተሰኘ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ የካቲት 1/2011 ዓ.ም ለሁሉም ኅብረተሰብ በይፋ ተከፍቷል፡፡

4

በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት በሙዚቃ ተመራማሪው አቶ ሰርፀ ፍሬስብሐት የ1888 ወርሃ የካቲት የአድዋ ድልና ሥነ ጥበብ በሚል ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢያን ካምቤል እና አቶ እንዳለጌታ ከበደ የ1929ኙን የየካቲት ጭፍጨፋ አስከፊነትና የተደረገውን ተጋድሎ፤ እንዲሁም በአቶ አሰግደው ሽመልስ የ1966ቱ የአብዮት መፈንዳትና የአገሪቱን የፖለቲካ ምስቅልቅል የተመለከተ ጽሁፎች ለታዳሚዎች አቅርበዋል፤ ውይይትም ተደርጎባቸዋል፡፡

2

ከውይይቱም በማስቀጠል በብላቴንጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል የተሰናዳው ዐውደ ርዕይ በታዳሚዎች ተጎብኝቷል፡፡

1

ዐውደ ርዕዩ ከየካቲት 1 – 30/2011 . ድረስ ለኅብረተሰቡ ክፍት ይደረጋል፤ ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ቀኑን ሙሉ በማዕከሉ በመገኘት ሁሉም ኅብረተሰብ እንዲጎበኘው አካዳሚያችን ጥሪ ያደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *