ሙያዊ ገለጻና ውይይት ተከናወነ

የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ትውፊትና ጓዞቹ በሚል ርእስ በመምህር ሔኖክ ያሬድ ሙያዊ ገለጻና ውይይት ተከናውኗል፡፡

የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ባዘጋጀው መደበኛ ሙያዊ የገለጻና የውይይት መድረክ ላይ ስለባሕረ ሐሳብ ምንነት፣ የኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ ፍልስፍና እና ይዘት በሰፊው ትንታኔ በባለሙያው ተሰጥቶ በተነሱ ነጥቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ይኽ ጥንታዊ የባሕረ ሐሳብ ጥበብ እምነትን (የክርስትና፣ የእስልምና፣ የአይሁድ እንዲሁም የሌሎች) የዘመን መስፈሪያ ልማዶችን ያቀፈ የጸሐይ፣ የጨረቃ እና የክዋክብትን እንቅስቃሴ ያካተተ መሆኑን አቅራቢው አመላክተዋል።

አቅራቢው አያይዘው በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ መረዳት ውስጥ ሊዳብሩ፣ ከእውቀት እና መረጃ ማነስ ምክንያት የሚፈጠሩ የተዛቡ እይታዎች ሊታረሙ ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

በገለጻና ውይይት መድረክ ላይ የአካዳሚው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳት ያለም ፀሓይ መኮንን፣ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ፣ የአካዳሚው አባላት፣ በርካታ የሥነ ጥበባት ባለሙያዎች፣ ሌሎች ታዳሚያን እና የመገናኛ ብዙኃን ተሳትፈዋል።

ይኽ ሙያዊ የውይይት መድረክ ቅዳሜ በየአስራ አምስት ቀኑ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ይከናወናል።

የፊታችን ቅዳሜ ጳጉሜ 4 ቀን 2015 ዓ.ም.  ደግሞ በዛጎል መጽሐፍ ባንክ አዘጋጅነት በማዕከሉ አስተባባሪነት የሚሰናዳው #ነገረ_መጻሕፍት የተሰኘው ዝግጅት ደራሲ ሕይወት_ተፈራን በመጋበዝ “#በምንትዋብ” መጽሐፏ እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከእንዳለ ጌታ ከበደ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ይካሄዳል፡፡

ሁላችሁም ከወዲሁ በአክሮት ተጋብዛችኋል፡፡

አድራሻ፦ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡

ለበለጠ መረጃ እና መገኘትዎን ለማረጋገጥ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡

https://t.me/+VZQIhKm-NoAwYjM0

በራሳችሁ ለምትመጡ አድራሻው Ethiopian Academy of Sciences

https://maps.app.goo.gl/GwKfjcwg1jmqsfG76

እንዲሁም 0777664020 ይደውሉ፡፡

ድረ ገጽ፦ https://eas-et.org/

ፌስቡክ፡- (20+) Facebook