የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሳይንሳዊ ገለጻና ውይይት መድረክ
በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ወርሐዊ ገለጻና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
የዚህ ወር የገለጻና ውይይት መድረክ ሐሙስ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከ11፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ‘‘የአየር ብናኝ ብክለት በጤና ላይ የሚያስከትለው ችግር” በተሰኘ ርእስ በፕሮፌሰር አበራ ቁሜ አቅራቢነት በፕሮፌሰር አለማየሁ ወርቁ አወያይነት ገለጻ ይደረጋል።
ገለጻና ውይይቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲሁም ከታች በተጠቀሰው የዙም አድራሻ በቀጥታ እንድሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
https://us06web.zoom.us/j/83253374239?pwd=VFpLenBSS0NLbEFGL213YWR4aDI3UT09
Meeting ID: 832 5337 4239
Passcode: 921303