ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ አካዳሚያዊ እና ሳይንሳዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ወርሐዊ ሳይንሳዊ ገለፃና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየዉን ይህንኑ መርሐ ግብር በየወሩ ለማስቀጠል መጪው ዓርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ “ፌዴራሊዝምና ጎሣዊ አደረጃጀት፣ ከኢትዮጵያ ተሞክሮ ምን ትምህርት ተገኘ?” በተሰኘ ርዕስ ላይ ሳይንሳዊ ገለጻና ውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡

በመድረኩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶክተር ያቆብ አርሳኖ  ገለጻ ያደርጋሉ። 

የውይይቱ አይነት በከፊል በአካል ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግቢ በዶክተር እሸቱ ጮሌ አዳራሽ እንዲሁም በበይነ መረብ ይተላለፋል፡፡

ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል!