ኢ.ሳ.አ. በአገሪቱ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎችንና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማትን ለማሳደግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የኢፌዴሪ የሳይስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ወደ እውቀት-መር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 5 እስከ 8 /2013 ዓ.ም የተካሄደው የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን (HEART CONVENTION 2021) ይፋዊ የማጠቃለያ ስነስርዓት  በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚው ቅጥር ግቢ በተካሄደበት ወቅት ነበር፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘዉም፣ አካዳሚው በዋነኛነት እየሠራበት ያለው ሳይንስን ባህል በማድረግ በእዉቀት፣ በክህሎት እና በጥበብ የበለጸገ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር መደራደር የሚችል ማህበረሰብ የመፍጠር ተግባር ወሳኝነት እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡

 ዝርዝሩን ለመመልከት ይህን ይጫኑ