የ‘‘UNIDO’’ እና የ ‘‘CIRHT’’ የሥራ ሓላፊዎች ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር ተወያዩ

የተባበሩት መንግሥታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (United Nation Industrial Development Organization (UNIDO) እና Center for International Reproductive Health Training (CIRHT) የተሰኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በትብብር በሚስሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡

በአካዳሚው ጽ/ቤት በተካሄደው የሁለቱ ተቋማት እና የአካዳሚው የስራ ሓላፊዎች ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ-ማርያም እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ ስለ አካዳሚው ዋና ዋና የሥራ መርሃ ግብሮች፣ እየሠራቸው ስላሉ ሥራዎች እና በትብብር ሊሠሩባቸው ስለሚችሏቸው ጉዳዮች ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

ከገለጻው በኋላ ውይይት ተካሂዶ ወደፊት በትብብር  በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።

በመጨረሻም ጎብኝዎቹ  የአካዳሚውን የሳይንስ ማእከል የተለያዩ ኤግዚቢቶችን እና የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ አካዳሚው የሳይንስ እውቀትና ባህልን ለማኸዘብ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጭ ጅምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡