ዓድዋና ኪነጥበብ ሙያዊ ገለጻና ውይይት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ የገለጻና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

አካዳሚው 129ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ዓድዋና ኪነጥበብ” የተሰኘ ሙያዊ  ገለጻና ውይይት ያካሂዳል።

መርሐግብሩን የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሽፈራሁ በቀለ ይመሩታል።

  • እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር) – (ዓድዋና ሥነጽሑፍ)
  • ሰአሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን -(ዓድዋና ሥነጥበብ)
  • ትዕግሥት ዓለማየሁ – (ዓድዋና ቴአትር እና ሲኒማ)
  • ሰርጸ ፍሬስብሀት – (ዓድዋና ሙዚቃ)

በየዘርፋቸው መወያያ ሐሳቦችን ያቀርባሉ።

መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ  ሐሙስ የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።