በአክብሮት ተጋብዘዋል!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ  የፓናል ውይይት መድረክ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን  ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
አሁንም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሐግብሮች አንዱ የኾነውን የፓናል ውይይት “የኢትዮጵያን የምልክት ቋንቋና መስማት የተሳናቸው ማኅበረሰቦችን ለአካታች ልማትና ኅብረተሰብ ማብቃት” በተሰኘ ርእስ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።



አቅራቢዎች 

  •   ዶክተር ኢያሱ ኃይሉ
  •  ዶክተር ጳውሎስ ካሱ
  • ዶክተር አንዳርጋቸው ደነቀ
  •  አቶ ዓለማየሁ ተፈሪ

አወያይ፡-  ዶክተር መኮንን ሙላት
 መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ  ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
አካዳሚው