የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
አሁንም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሐግብሮች አንዱ የኾነውን የፓናል ውይይት “የአየር ንብረት ብክለት በአፍሪካ ጤና እና ምጣኔ ሀብት ላይ የደቀነው ስጋት”፣ (Air Pollution as a Threat to Health and Economic Growth in Africa) በተሰኘ ርእስ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።
አቅራቢዎች፡-
- ዶክተር አርአያ አስፋው
- ፕሮፌሰር ሰለሞን ቢልልኝ
- ፕሮፌሰር አበራ ኩሜ
- አቶ አሸናፊ በረደድ
አወያይ፡- አቶ ጥበቡ አሰፋ
መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት (April 10, 2025, from 4:00 p.m. to 6:00 p.m.) ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው ወይም ከዚኽ በታች በተጠቀሰው የዙም አድራሻ በቀጥታ እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
Join Zoom Meeting
Link: https://us06web.zoom.us/j/84982334618?pwd=maN1yz0QD7fRzY9aS24twSnaafToaI.1
Meeting ID: 849 8233 4618
Passcode: 831700