በአክብሮት ተጋብዘዋል

በግብርና ምርምር ተቋም መሥራች፣ አደራጅ እና መሪነታቸው የሚታወቁትን የዶ/ር ስሜ ደበላን አበርክቶዎች የሚዘክረው በደራሲ ገስጥ ተጫኔ የተጻፈው “ስሜ ደበላ፤ ታላቁ የግብርና ምርምር ሥርዓት መሪ” የተባለው መጽሐፍ ቅዳሜ መጋቢት 6፣ 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ይመረቃል። በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የዶ/ር ስሜ ደበላ ሕይወት እና አበርክቶዎች በተለያዩ ዝግጅቶች ይዘከራሉ።
በመሆኑም በመጽሐፍ ምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ እንዲገኙልን በአክብሮት ጋብዘንዎታል።