በአክብሮት ተጋብዘዋል!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ ማእከል “የኑክሊየር ኃይል ጥቅሞችና አስፈላጊነት” በሚል ርእስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፊዚክስ ትምህርት ክፍል የኑክሊየር ኃይል ሳይንቲስት በዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ አቅራቢነት ሳይንሳዊ ገለጻ ያካሂዳል።

መርሐግብሩ ቅዳሜ፣ ታህሣስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 – 10፡00 ሰዓት በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
አድራሻ:- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ ወይም በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ።
የጉግል ካርታ፡- https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217