የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከዋልያ መጻሕፍት ጋር በመተባበር “መንግሥትና ሀብት” በተባለው የዶ/ር ብርሃኑ በሻህ መጽሐፍ መነሻነት የፓናል ውይይት አዘጋጅቷል፡፡ በውይይቱ ላይ የአገር ሀብት ነጻነት፣ የመዋቅር ለውጥ፣ ግሽበት፣ የሰው ሀብት ልማት፣ ባህል እና የአካባቢ ጥበቃን ስለመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮች ባለሙያዎች ገለጻዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
በውይይቱ ላይ እንድትገኙ በአክብሮት እየጋበዝን፣ በዕለቱ “መንግሥትና ሀብት” መጽሐፍን በቅናሽ ለገበያ ይቀርባል፡፡
ቀን፡ ዓርብ ሚያዝያ 3፣ 2017 ዓ.ም
ቦታ፡ ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ፤ ኢኽላስ ሕንፃ፣ አራት ኪሎ ከአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ጀርባ