ባዮቴክኖሎጂያዊ የፍሳሽ ውሃ ሕክምና ሂደት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‹‹ባዮቴክኖሎጂያዊ የፍሳሽ ውሃ ሕክምና ሂደት›› በተሰኘ ርዕስ የሳይንሳዊ ገለጻና ውይይት መድረክ ሐሙስ ግንቦት 29/2011 ዓ.ም ከ11፡00 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ (4 ኪሎ ግቢ፣ ቅድስት ሥላሴ ፊት ለፊት) 5ኛ ፎቅ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

በዚህ የሳይንሳዊ ገለጻና ውይይት መድረክ ደቂቅ-ዘአካላትን በማሳተፍ ውጤታማ የሆኑ ባዮቴክኖሎጂያዊ የፍሳሽ ውሃ ሕክምና ሂደትን የሚዳስስ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፡፡

በውይይቱ፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የመንግስት ተቋማት፣ የብዙኃን መገናኛ አካላት፣ ተመራማሪዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እንዲሁም ኅብረተሰቡ ይሳተፋሉ፡፡ እርስዎም በውይይቱ ላይ በመገኘት ውይይቱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በማክበር ጋብዘናል፡፡

 

Date
End Date
Location
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ (4 ኪሎ ግቢ፣ ቅድስት ሥላሴ ፊት ለፊት) 5ኛ ፎቅ